ፍኖት አንብቦ መረዳት ክህሎት የሚያሳድግ የንባብ ፕሮግራም ነው። የመማሪያ መፅሃፍ እና 12 አጋዥ መፅሃፍት አሉት ።
መጽሐፉ ስድስት ትምህርት (lessons) ሲኖሩት መጽሐፋችን ጀማሪ አንባቢ ልጆቻችንን የሚከተሉትን የንባብ ችሎታዎችን ያስተምራል።
1 ዋና ሃሳብ 2. ገፀባህርይ 3. መቼት 4. ትልም 5. ምክንያት እና ውጤት እና 6. ማመሳሰል እና ማነፃፀር
ይህ ፕሮግራም የልጆቻችን አቅም ባገናዘበ መልኩ የቀረበ ነው። እያንዳንዱ ትምህርት የመጻፍ፣ የመናገር እና አንብቦ የመረዳት ችሎታን የሚያዳብሩ መልመጃዎች እና 12 ምንባቦች አሉት። ንባቦቹ ልብወለድ፥ ኢ ልብወለድ ፥ ፋንታሲ፥ እና የመረጃ ፅሁፎች አሉት።
እያንዳንዱ ትምህርት የመጻፍ፣ የመናገር እና አንብቦ የመረዳት ችሎታን የሚያዳብሩ መልመጃዎች እና ሁለት ምንባቦች አሉት። ታሪኮቹን ካነቡ እና መልመጃዎን ከሰሩ በኋላ ተማሪዎች ትስስርን ይፈጥራሉ። ትስስር ምንድን ነዉ ? ልጆች የተማሩት ሀሳብ ከራሳቸው፣ ከአካባቢያቸው እና ከአለም ጋራ እንዴት እንደሚገናኝ ካልተረዱ ምኑን ተማሩት?
ስለዚህ ይህ የሚዳቆ መፅሃፍ ተማሪዎች አንድን ትምህርት * ከራስ ጋር * ፅሁፍን ከፅሁፍ ጋር እና * ትምህርትን / ፅሁፍን ከአለም ጋር እንዲያስተሳሩ ያግዛል።
እያንዳንዱ ትምህርት ሲያልቅ ሁለት አጋዥ መጽሐፍት አሉት ። አንብበውም አያቆሙም- ሪፖርት ይፅፋሉ።
እንደሁልጊዜው መፅሃፋችን በጥናት እና በሙከራ ላይ ተመስርቶ ነው የተዘጋጀው። በሙከራችን ላይ እንዳየነው ከሆነ ልጆች መልመጃዎቹን በደስታ፣ በመነጋገር፣ በትኩረት እና በመረዳዳት ስሜት ተሞልተው ነበር።
የልጆቻችንን እምቅ ተፈጥሯዊ ችሎት በጋራ እናዉጣ።
Reviews
There are no reviews yet.