midaqo

ፈጠራ የታከለበት የአማርኛ ማስተማሪያ (innovative Amharic learning resources)

$55.00

Category:
ይህ ፈጠራ የታከለበት የማስተማሪያ ዘዴ በድምፅ(phonic) እና የቃላት ድግግሞሽን(iterative patter recognition) በመጠቀም የአማርኛ ፊደላትን በተሻለ ፍጥነት ለይቶ ለማወቅና ለማንበብ ያስችላል፡፡ አዲሱ ዘዴ ለዚሁ ዓላማ በድርጅታችን በተዘጋጁ የመማሪያ መፅሐፍት፤ የመምህሩ መመሪያ፤ እና ሐምሳ(50) የንባብ መለማመጃዎች / ተነባቢ መፅሐፍት (decodables)፡፡ ድርጅታችን ሚዳቆ ከተለመደው በተለየ ይህን አዲስ የማስተማሪያ ዘዴ የሚተገብርበት የራሱ አሰራርና አካሄድ አለው፡፡ በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ከ34ቱ ቀዳሚዎቹን ሆሄያት ማለትም የግዕዝ ቤተሰቦችን(ሀ፣ለ፣ሐ…) ብቻ በመለየት ተማሪዎች እንዲያውቋቸው ይደረጋል፡፡ ተማሪዎቹ በነዚህ የፊደል ቤተሰቦች የተፃፉ 10 መፅሐፍትን እያነበቡ ፊደላቱን በቀላሉ ያውቋቸዋል፤ ያነቧቸዋልም፡፡ በዚህ መልኩ እየተማሩ 12 ቀዳሚ ሆሄያት ፊደላትን አጥርተው ከተረዱ በኋላ ደረጃ 1 መፅሐፍ 1 ን ያነባሉ፡፡ በመጀመሪያው ንባብ ላይም ልጆች ፊደላት የሚማሩት በምክንያት መሆኑን ተረድተው ሌሎች ፊደላትንም ለማወቅና ለመጠቀም ያላቸው ጉጉት ይጨምራል፡፡ ተማሪዎቹ የግዕዝ የፊደል ቤተሰቦችን ከተማሩ በኋላም በቀጣይ የካብዕ ሆሄያትን (ሁ፣ሉ፣ሑ…) ይማራሉ፡፡ በሚዳቆ አዲሱ የማስተማሪያ ስልት መሰረትም የካብዕ ሆሄያትን የድምፅና የቅርፅ መለያዎች ይማራሉ፡፡ እነዚህ መለያዎችም የ ካብዕ ፊደላት ሲነበቡ የ “ኡ” ድምፅ እንዳላቸውና ቅርፃቸው ላይም ከግዕዝ በቀላሉ የሚለዩባቸውን ሁኔታዎች ይረዳሉ(Phonic awareness and iterative pattern recognition)፡፡ ይህም የካብዕ ፊደላት የሚፈጠሩት በግዕዝ ፊደላት ቅርፅ ላይ ከላይ እና ከጎን ጭረት በማድረግ መሆኑን ልብ እንዲሉና በቶሎ እንያውቁ ያስችላል፡፡
የካብዕ ፊደላትን እየለዩና በነዚሁ ፊደላት የተዘጋጁላቸውን መፅሐፍት እያነበቡ በመለማመድ ፊደላቱን አጥርተው እንዲያውቁ ይደረጋል፡፡ ቀሪዎቹን አምስት የፊደል ቤተሰቦችም (ሂ፣ሃ፣ሄ፣ህ፣ሆ…) በዚህ መንገድ በመማሪያ መፅሐፋችን፤ በሐምሳ ተነባቢ መፅሐፍት (decodables) በመታገዝ ከ አምስት እስከ ስምንት ወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ አማርኛን ማንበብን ይማራሉ፡፡
Weight 1 kg

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “ፈጠራ የታከለበት የአማርኛ ማስተማሪያ (innovative Amharic learning resources)”

Your email address will not be published. Required fields are marked *